Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ዛሬ በ3 የማጣሪያ ውድድሮች ትሳተፋለች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውን ሴቶች አትሌቶች የሚሳተፉበት የ800 ሜትር፣ 5 ሺህ ሜትር እንዲሁም 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ይካሄዳል፡፡

ከረፋዱ 5፡05 ላይ የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ፣ ምሽት 2፡02 ላይ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ እንዲሁም ምሽት 2፡53 ላይ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ይካሄዳል፡፡

በ800 ሜትር የማጣሪያ ውድድሩ ÷ አትሌት ሀብታም ዓለሙ፣ አትሌት ወርቅነሽ መለሰ እና አትሌት ትዕግስት ግርማ ይሳተፋሉ፡፡

እንዲሁም በ5 ሺህ ሜትር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ አትሌት መዲና ኢሳ፣ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ እና አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በ3 ሺህ ሜትር የመሰናክል የማጣሪያ ውድድር አትሌት ሎሚ ሙለታ፣ አትሌት ሲምቦ አለማየሁ እና አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ይሳተፋሉ፡፡

በሜዳሊያ ሰንጠረዡ÷ ኢትዮጵያ 1 የወርቅ፣ 3 የብር እንዲሁም 2 የነሐስ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከዓለም በሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

አሜሪካን እና እስፔን በቅደም ተከል የደረጃ ሰንጠረዡን እየመሩ ይገኛሉ፡፡

በሀንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ የሚገኘው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ አምስተኛ ቀኑን ይዟል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.