Fana: At a Speed of Life!

የ5ሺህ ሜትር የአትሌቶች ለውጥ ውሳኔ ውጤት ለማምጣት ያለመ ነው – ፌዴሬሽኑ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ5ሺህ ሜትር የአትሌቶች ለውጥ ውሳኔ ውጤት ለማምጣት ታሰቦ የተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

በ5ሺህ ሜትር አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ተቀንሶ በምትኩ አትሌት በሪሁ አረጋዊ እንዲሮጥ መወሰኑን ተከትሎ አትሌት ጥላሁን ሀይሌ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ቅሬታ ማሰማቱ ይታወሳል፡፡

ጉዳዩን በማስመልከትም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች ከሀንጋሪ ቡዳፔስት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ÷ አትሌት ጥላሁን ሀይሌ በ5ሺህ ሜትር ጥሩ ሰዓት ቢኖረውም ከወቅታዊ ብቃት ጋር በተያያዘ አትሌት በሪሁ አረጋዊ በርቀቱ የተሻለ ሆነ መገኘቱን ገልፀዋል፡፡

በግል ሰዓታቸው የግል ሚኒማ መሰረት አትሌት ጥላሁን ሀይሌ በርቀቱ ከሚሳተፉ አትሌቶች የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡

በዚህም እንደ ሀገር ውጤት ለማምጣት በ5ሺህ ሜትር አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ተቀንሶ በምትኩ አትሌት በሪሁ አረጋዊ እንዲሮጥ ፌዴሬሽኑ መወሰኑን ፕሬዚዳንቷ አብራርተዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.