Fana: At a Speed of Life!

ዓባይ ባንክ አ.ማ እና ሳፋሪኮም ኤምፔሳ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓባይ ባንክ አ.ማ ከሳፋሪኮም ኤምፔሳ ጋር ስትራቲጂክ የሥራ አጋር በመሆን አብረው ለመሥራት  የሥራ  ስምምነት ውል ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱም ዓባይ ባንክ የሳፋሪኮም ኤምፔሳ ሱፐር ኤጀንት በመሆን የሞባይል ባንኪንግ እና የኤጀንት ባንኪንግ ሥራዎችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማሳለጥ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም ÷ደንበኞች ከዓባይ ባንክ ወደ ኤምፔሳ ወይም ከኤምፔሳ ወደ ዓባይ ባንክ ገንዘብ ማስተላለፍ እንዲችሉ፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን እንዲከፍሉ፣ የሒሳብ መረጃዎችን እንዲያዩ፣ የአየር ሰዓት እንዲገዙ እና ሌሎችንም የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የተቋማቱ አመራሮች የተጀመረውን የሥራ አጋርነት ስምምነት በማጠናከር ደንበኞችን የዘመናዊ የባንክ አገልግሎት እና የክፍያ ሥርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር እንደሚሠሩ ስምምነቱን በፈረሙበት ወቅት አረጋግጠዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.