Fana: At a Speed of Life!

ሽመልስ በቀለ መቻልን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ጷጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሀገር ውጭ በተለያዩ ሀገራት ክለቦቸ ለ10 ዓመታት ሲጫወት የቆየው ሽመልስ በቀለ ለመቻል ፈርሟል፡፡

የብሄራዊ ቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ወደ ግብፅ ያመራ ሲሆን÷ በግብፅ ለሚገኙ ሶስት የተለያዩ ክለቦች መጫዎች ችሏል፡፡

በፔትሮጀት ስድስት ዓመታትን፣በምስሪ ላል መቃሳ ሁለት ዓመታትን በኤል ጎውና ለአንድ ያመት ያህል በተመሳሳይ በኢ ኤን ፒ ፒ አይ  አንድ ዓመት ማሳለፍ ችሏል፡፡

ቀሪ አንድ አመት ኮንትራት እየቀረው ከኢ ኤን ፒ ፒ አይ   የተለያየው ሽመልስ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ በዛሬው እለት  በሁለት ዓመት ውል መቻልን መቀላቀሉን ሶከር ኢትጵያ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.