Fana: At a Speed of Life!

በኦንላይን ከ400 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ400 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በኦንላይን መስጠቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጡን በሀገር አቀፍ ደረጃ በኦንላይን ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 401 ሺህ 830 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን በኦንላይን መስጠት መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡

አገልግሎቱ ከፌዴራል እስከ ክልል ባሉት የንግድ ተቋማት የተሰጠ መሆኑንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በኦንላይን ከተሰጡ አገልግሎቶች መካከል የንግድ ምዝገባ፣ አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ፈቃድ እድሳት፣ የንግድ ስራ ፈቃድ ስረዛና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

የኦንላይን አገልግሎቱ የደንበኞችን እንግልት ከማስቀረት ባለፈ ወጪና ጊዜያቸውን መቆጠብ ማስቻሉ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.