Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የቴሌ ብር መልካም ተሞክሮን በሞባይል ዓለም አቀፍ ኮንግረስ ላይ አካፈለች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የቴሌ ብር መልካም ተሞክሮን በሞባይል ዓለም አቀፍ ኮንግረስ 2023 የፊንቴክ ስብሰባ ላይ አካፍላለች፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በሩዋንዳ ኪጋሊ እየተካሄደ በሚገኘው የሞባይል ዓለም አቀፍ ኮንግረስ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በዛሬው ዕለት ቴሌብር በኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እያፋጠነ እንደሚገኝ መልካም ተሞክሮውን በመድረኩ ማጋራታቸውን የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ቴሌብር በኢትዮጵያ እያስመዘገበ የሚገኘው ስኬት የሞባይል ቴክኖሎጂ የአህጉሪቱን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን እና ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.