Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የስፔን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት የሶስት አመት ዕግድ ተላለፈባቸው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በቀድሞው የስፔን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቢያሌስ ላይ ዕገዳ አስተላለፈ።

ፊፋ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከማንኛውም ስፖርታዊ ጉዳዮች ለሶስት አመታት እንዲታገዱ ነው ውሳኔ ያሳለፈው።

ሩቢያሌስ ስፔን አሸናፊ በሆነችበት የሴቶች የዓለም ዋንጫ የሽልማት ሥነ ሥርአት ላይ የቡድኑን አጥቂ ሄኒ ሄርሞሶን ከንፈር በመሳማቸው ምክንያት በፊፋ በጊዜያዊት ታግደው ጉዳያቸው ሲታይ ቆይቶ ነበር።

ከፊፋ ዕግድ በኋላም ባለፈው መስከረም ወር ከሃላፊነት መነሳታቸውም የሚታወስ ነው።

ፊፋም ግለሰቡ የፊፋን የሥነ ምግባር ኮድ አንቀጽ 13ን በመጣሳቸው የሶስት አመት ዕግድ እንደተወሰነባቸው አስታውቋል።

ግለሰቡ ድርጊቱን ከፈጸሙ በኋላ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ድርጊቱ ‘በጋራ ሥምምነትና መግባባት’ የተፈጸመ ነው በማለት ለማለፍ ቢሞክሩም፥ ተጫዋቿ ግን ድርጊቱ ከፍላጎቴ ውጭ ነው በሚል ግለሰቡን ከሳቸው ነበር።

ፊፋ ባወጣው መግለጫ የ46 አመቱ የቀድሞ የስፔን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት ‘ድርጊቱን በፍላጎትና ተነሳሽነት ፈጽመውታል’ በማለት የዕግድ ውሳኔ ማሳለፉን ቢቢሲ አስነብቧል።

ግለሰቡ በፊፋ የሥነ ምግባር ኮሚቴ ውሳኔ ላይ ተቃውሟቸውን ለፊፋ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችሉም ታውቋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.