Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ በተካሄደ ኢንተርናሽናል ማርሻል አርት ውድድር ኢትዮጵያ 3ኛ ደረጃን ያዘች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦርላንድ ፍሎሪዳ ከተማ በተካሄደው ኢንተርናሽናል ማርሻል አርት ፌስቲቫል እና ውድድር ኢትዮጵያ በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች፡፡

ሦስት ወርቅ እና አንድ የነሐስ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ነው ኢትዮጵያ በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ውድድር ከአሜሪካ እና ስኮትላንድ በመቀጠል ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀችው፡፡

ኢትዮጵያ በነፃ ፍልሚያ እና በፓተርን ውድድሮች የተሳተፈች ሲሆን÷ ኤልያስ ኩመል በፓተርን እና ነፃ ፍልሚያ ከ 63 እስከ 69 ኪሎ ግራም ባደረገው ውድድር ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግቧል፡፡

እንዲሁም ወንድወስን ብርሃኑ በነፃ ፍልሚያ ከ75 እስከ 80 ኪሎ ግራም የወርቅ እና በፓተርን የነሐስ ሜዳልያ ማስመዝገቡን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከጥቅምት 16 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ በውድድር 17 ሀገራት ተሳትፈዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.