Fana: At a Speed of Life!

ነገ የፋና ላምሮት የፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ የፋና ላምሮት ምዕራፍ 15 የፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል።

ላለፉት 8 ሳምንታት በዳኞችና በራሳቸው ምርጫ ሲወዳደሩ የነበሩት መቅደስ ዘውዱ፣ ሀይለየሱስ እሸቱ፣ ሄኖክ ብርሃኑ እና ኪሩቤል ጌታቸው ነገ ከኮከብ ባንድ ጋር በ3 ዙር በሚያደርጉት ውድድር ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለተወዳዳሪዎች የ 1 ሚልየን ብር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን÷ በሚያገኙት ደረጃ የ400ሺህ፣ የ300 ሺህ፣ የ200 መቶ ሺህ እና የ100 ሺህ ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።

በነገው ደማቅ የፍፃሜ ውድድር ላይ አንድ ድምፃዊ በክብር እንግድነት ይገኛል።

ከ2011 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ አሁንም ድረስ በድምቀት የቀጠለው ፋና ላምሮት የባለተሰጥኦ ድምፃውያን ውድድር በዓመት ውስጥ የአሸናፊዎች አሸናፊን ጨምሮ አራት ምዕራፎችን ያካሂዳል።

እያንዳንዱ ምዕራፍ ለዘጠኝ ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን÷ በሶስት የተለያዩ ምዕራፎች ከ1 እስከ 4ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ ተወዳዳሪዎች በአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር አንድ ላይ ይገናኛሉ።

በውድድር ላይ በሚያሳዩት ብቃት ላይ የተመሰረተው ፋና ላምሮት ከሚሰጠው የገንዘብ ሽልማት በላይ ለተወዳዳሪዎች ቀጣይ የሙዚቃ ጉዞ መነሻ መሆን የቻለ ነው።

ተወዳዳሪዎችም በአድማጭ ተመልካች ዘንድ እውቅና እንዲያገኙ አድርጓል።

ነገ የምዕራፍ 15 የፍፃሜ ውድድርን በፋና በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች፣ በፋና ቴሌቪዥንና በሁሉም የኤፍኤም ጣቢያዎዎቻችን በቀጥታ ስርጭት እየተከታተላችሁ 8222 ላይ በእለቱ በሚገለፀው የድምፃውያን ኮድ በመላክ መደገፍ ትችላላችሁ።

በለምለም ዮሐንስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.