Fana: At a Speed of Life!

አማራጭ ወደቦችን ለመጠቀም የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኢትዮጵያ አማራጭ ወደቦችን ለመጠቀም እያደረገች ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገነዘበ፡፡

በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሸዊት ሻንካ የተመራ ቡድን የሞጆ ሎጅስቲክስ ማዕከል ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ከጎበኘ በኋላ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን እቅድና አፈፃፀም ገምግሟል፡፡

ወደብ ለኢትዮጵያ የኅልውና ጉዳይ መሆኑን ያስገነዘቡት ወ/ሮ ሸዊት÷ አማራጭ ወደቦችን ለመጠቀም የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መግለጻቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።

የባሕር ትራንስፖርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወሳኝ በመሆኑ የማሪታይም ባለስልጣን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሠራት እንዳለበትም ተመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አብዱልበር ሸምሱ÷ የሞጆ ሎጅስቲክስ ማዕከል ግንባታን በሚመለከት የሲሚንቶ እጥረት በፕሮጀክቱ አፈጻጸም ላይ መስተጓጎል መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.