Fana: At a Speed of Life!

የህብረት ስራ ማህበራት ቁጥራቸውን የሚመጥን ስራ እየተሰራ እንዳልሆነ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ያሉ የህብረት ስራ ማህበራት ቁጥራቸውን የሚመጥን ስራ እየተሰራ እንዳልሆነ የኢትዮጰያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ቀን በኢትዮጵያ ሕዳር 27 ቀን 2016 እንደሚከበር አስታውቋል።

የቀኑን መከበር አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ÷ ቀኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ75ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ2ኛ ጊዜ እንደሚከበር ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ከ23 ሺህ በላይ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን÷ ተቋማቱ ከ8 ሚሊየን በላይ አባላት በማፍራት ከ50 ቢሊየን በላይ ገንዘብ ከአባላት መሰብሰብ እንደቻሉ ተገልጿል፡፡

በየዓመቱም ከ15 ቢሊየን ብር በላይ ብድር የማቅረብ አቅም መፍጠራቸውም ተጠቁሟል፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ በመግለጫቸው÷ በኢትዮጵያ ያሉትን ህብረት ስራ ማህበራት ቁጥር በሚመጥን ልክ ስራዎች እየተሰሩ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ ካሉ መሰረታዊ ችግሮች መካከል ገበያውን ከማረጋገት እንፃር በትኩረት እንደሚሰራም መግለጻቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ቀኑ የቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበራት ከማስተዋወቁ ጎን ለጎን ለልምድ ልውውጥ፣ ጠቀሜታቸውንና ተደራሽነታቸውን ለማስፋት እንዲሁም እያከናወኑ ላሉት ስራም እውቅና መስጠት አላማ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.