Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል፡፡

ዛሬ 9፡00 ሰአት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስቴዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የድል ጎሎች ባሲሩ ኡመር እና ሲሞን ፒተር በ60ኛ እና በ83ኛ ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥሩ አለን ካይዋ ደግሞ የሻሸመኔ ከተማን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰአት ላይ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ከድሬዳዋ ከተማ ተገናኝተዋል።

ጨዋታው በድሬዳዋ ከተማ 2 ለ 0 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ቻርልስ ሙሴጌ የድል ጎሎቹን አስቆጥሯል።

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.