Fana: At a Speed of Life!

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ወደ አሸናፊነት ሲመለስ ዌስትሃም በሰፊ የጎል ልዩነት ተሸንፏል

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

11 ሰአት ላይ በተደረጉት ጨዋታዎች ኤቨርተን ከቼልሲ፣ ፉልሃም ከዌስትሃም ዩናይትድ እንዲሁም ሉተን ታዎን ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ተገናኝተዋል።

ከፋይናንስ ህግ ጥሰቶች ጋር በተያያዘ 10 ነጥቦች የተቀነሱበት የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን በሜዳው የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ቼልሲን አስተናግዶ ድል ቀንቶታል።

ጨዋታውን ኤቨርተን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ የድል ጎሎቹን አብዱላሂ ዶኮሬ እና ዶቢን አስቆጥረዋል።

በክራቨን ኮቴጅ ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናገደው ፉልሃም ደግሞ ጨዋታውን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

ጂሚኔዝ፣ ዊሊያን፣ ቶሲን፣ ዊልሰን እና ካርሎስ ቪኒሺየስ ለፉልሃም የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ከሜዳው ውጭ ከሉተን ጋር የተጫወተው የአምናው ሻምፒዮን ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ በበርናንዶ ሲልቫ እና ጃክ ግሪሊሽ ጎሎች ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።

ጨዋታውን ሲቲ 2 ለ 1 ሲያሸንፍ አደባዮ የሉተንን ማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.