Fana: At a Speed of Life!

የተራዘመው የአዲስ አበባ ደርቢ ጨዋታ የሚካሄድበት ጊዜ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የ7ኛ ሣምንት ተስተካካይ ጨዋታ  ታኅሣስ 20 ቀን 2016 እንዲካሄድ ተወሰነ፡፡

ጨዋታው የሚካሄደው ከቀኑ 9:00 ላይ በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ መረጃ አመላክቷል፡፡

ቅዳሜ ሕዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄድ የነበረበት የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወቃል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.