Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ከክለቡ ጋር ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰርቢያዊው የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣን ኒኮላ ካቫዞቪች ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል፡፡

የክለቡ የአካል ብቃት አሰልጣኙ ማርኮ ቭላስቪችም ባስገቡት መልቀቂያ መሰረት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር መለያየታቸውን ክለቡ በሳምንታዊ የሬዲዮ ፕሮግራሙ ላይ አስታውቋል፡፡

ሁለቱ አሰልጣኞች ያለፉትን አምስት ወራት ቡድኑን ለቅድመ ውድድር ከማዘጋጀት ጀምሮ በሊጉ የስምንት ሳምንት ጉዞ ማደረጋቸውም ይታወሳል።

የዋና አሰልጣኙን ስንበት ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡና በነገው እለት የሚያደርገውን የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨምሮ የፕሪሚየርሊጉ ጨዋታዎችን በምክትል አሰልጣኙ እየተመራ እንደሚያደርግ ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ደካማ እንቅስቃሴን ያሳየው ኢትዮጵያ ቡና በስምንት ጨዋታዎች ስምንት ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተምጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.