Fana: At a Speed of Life!

ከ9ኛ እስከ 11ኛ ሳምንት የሚደረጉ የሊጉ መርሃ ግብሮች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን አይኖራቸውም ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ9ኛ እስከ 11ኛ ሳምንት የሚደረጉ የሊጉ መርሃ ግብሮች የሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደማይኖራቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ፡፡

ማህበሩ እንደገለፀው÷ የ9ኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች ረቡዕ ታህሳስ 24 መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ የቦታ ለውጥ አልተደረገባቸው፡፡

በመሆኑም ከ9ኛ እስከ 11ኛ ሳምንት ያለው የሊጉ መርሃ ግብሮች በአዳማ ከተማ – አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚደረጉ መሆኑን ማህበሩ አስታውቋል፡፡

በተያያዘም የሶስቱ ሳምንታት ጨዋታዎች ከዚህ በፊት በተገለፀው የቀጥታ ስርጭት ድልድል መሰረት የሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደማይኖራቸው ማህበሩ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር 180 የሊጉ መርሃ ግብሮችን በሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ለመስጠት ውል መግባቱ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.