Fana: At a Speed of Life!

አንድሬ ኦናና በካሜሩን ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ተካተተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በኮትዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ በሚሳተፈው የካሜሩን ብሔራዊ ቡድን ዝርዝር ውስጥ ተካትቷል፡፡

ኦናና በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሀገሩ ከአሰልጣኝ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በጊዜያዊነት ከብሔራዊ ቡድኑ ርቆ መቆየቱ  ይታወሳል፡፡

ካሜሩን በአጠቃላይ 27 ተጫዋቾችን ይፋ ያደረገች ሲሆን÷ የባየርን ሙኒኩ አጥቂ ማክሲም ቹፖ ሞቲንግ ባልታወቀ ምክንያት ከስብስቡ አለመካተቱ ተገልጿል፡፡

ዛምቦ አንጉይሳ፣ ካርሎስ ቶኮ ኢካምቤ፣ ቪንሴንት አቡበከር እና ፍራንክ ማግሪን የመሳሰሉ የወቅቱ ከዋከብቶች በብሄራዊ ቡድኑ መካተታቸው ታውቋል፡፡

የሶስት ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮኗ ካሜሩን በመጀምሪያ የምድብ ጨዋታ ከጊኒ ጋር በፈረጆቹ የፊታችን ጥር 15 ቀን ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡

በተመሳሳይ ሞሮኮ 27 ተጫዋቾችን ይፋ ያደረገች ሲሆን÷ አሺራፍ ሃኪሚ፣ ናየፍ አጉዌርድ፣ሶፊያን አምራባት፣ ዩሱፍ ኢል ነስሪ፣ ሃኪም ዚያች እና ሶፊያን ቡፋል የመሳሰሉ ከዋክብቶች በብሄራዊ ቡድኑ ተካትተዋል፡፡

ሞሪታኒያ እና ደቡብ አፍሪካ ቀደም ሲል በ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፈውን ብሄራዊ ቡድናቸውን ይፋ ያደረጉ ሲሆን ÷ ሌሎች ሀገራትም በቀጣይ ቀናት ቡድናቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ የካፍ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.