Fana: At a Speed of Life!

ምዕመኑ በዓለ ጥምቀቱን ሲያከብር ሐይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝበ ክርስቲያኑ የከተራና የጥምቀት በዓልን ሲያከብር ሐይማኖታዊ ሥርዓቱንና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት አሳሰበ፡፡

በዓለ ጥምቀቱ  በባሕርዳር ከተማ ሐይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር በቂ ዝግጅት መደረጉን የሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መላከ ሰላም ኤፍሬም ሙሏለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡

ሕዝበ ክርስቲያኑ የጥምቀት በዓልን ሲያከብርም ዕምነቱ በሚያዝዘው መሰረት በሰላምና በፍቅር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ሁሉም የዕምነቱ ተከታዮች የበዓሉ ዋና ባለቤቶች መሆናቸውን ተገንዝበው  በሰላምና በፍቅር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዓሉ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በባሕር ዳር ከተማ በጣና ዳርቻ መከበር መጀመሩንም አስታውሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.