በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
አስራ ሦስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና ድል ሲቀናው ሀድያ ሆሳዕና ከድሬደዋ ከተማ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያተዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና አንተነህ ተፈራ በ24ኛ፣ በ47ኛ እና 59ኛ ደቂቃ ላይ ጎሎችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችሏል፡፡