Fana: At a Speed of Life!

በቦስተን የኒው ባላንስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይና ለሜቻ ግርማ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦስተን የኒው ባላንስ የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ እና ለሜቻ ግርማ ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቀዋል፡፡

በ1 ሺህ 500 ሜትር የተወዳደረችው ጉዳፍ ፀጋይ ርቀቱን በ3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡

በዚሁ ርቀት የ18 ዓመቷ አትሌት ብርቄ ሀየሎም 3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

ወጣቷ አትሌት ብርቄ ሀየሎም በርቀቱ ያስመዘገበችው ሰዓት ከ20 ዓመት በታች የዓለም ፈጣኑ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በተመሳሳይ አትሌት ለሜቻ ግርማ የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድርን በ7 ደቂቃ 29 ሰከንድ ከ08 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ማሸነፉን የቦስተን ማራቶን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.