Fana: At a Speed of Life!

በግማሽ ፍጻሜ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ኮትዲቯር ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በግማሽ ፍጻሜ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ኮትዲቯር ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ዛሬ ምሽት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ ለፍጻሜ ለማለፍ የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 2 ሰዓት ላይ በአቢጃን ስታድ ዲ ላ ፔይክስ ይካሄዳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በግማሽ ፍጻሜ በታሪክ ለ4ኛ ጊዜ የተገናኙ ሲሆን÷ ያለፉት ሶስት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በንስሮቹ አሸናፊነት የተጠናቀቁ ናቸው፡፡

ንስሮቹ በአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ 15 ጊዜ ለግማሽ ፍጻሜ በመድረስ ቀዳሚ ሲሆኑ÷ በአንጻሩ ባፋና ባፋናዎቹ ደግሞ ለግማሽ ፍጻሜ የደረሱት አራት ጊዜ ብቻ ነው፡፡

በተመሳሳይ አዘጋጇ ኮትዲቯር ከዴሞክራቲክ ኮንጎ የሚያደርጉት የግማሽ ፍጻሜ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በአላሳን ኦታራ ስታዲየም ይደረጋል፡፡

ከምድብ ምርጥ ሶሰተኛ በመሆን ወደ ጥሎ ማለፉ የገባችው ኮትዲቯር ሴኔጋልን በመለያ ምት እንዲሁም ጊኒን በጨዋታ 2 ለ 1 በማሸነፍ ነው ሳትጠበቅ ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀለችው፡፡

በተመሳሳ በመድረኩ አስገራሚ ግስጋሴ እያደረገች የምትገኘው ዴሞክራቲክ ኮንጎ ግብጽ እና ጊኒን በመለያ ምት በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜ መድረሷ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.