Fana: At a Speed of Life!

የፊፋ ቴክኒካል ልዑክ ድሬዳዋ ገባ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ቴክኒካል ልዑክ ድሬዳዋ ከተማ ገብቷል፡፡

ልዑኩ ድሬዳዋ ከተማ የገባው የድሬዳዋ ስታዲየም የአርቴፊሻል ሳር ንጣፍ እድሳት መጠናቀቅን ተከትሎ ሙያዊ ምልከታ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በምልከታውም ስታዲየሙ የፊፋን መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን የማረጋገጥ ሥራ እንደሚያከናውን ይጠበቃል መባሉን የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.