Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት በተካሄደው 14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና ድል ቀንቷቸዋል፡፡

9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ጎሎች በዛብህ መለዮ እና ማይክል ኪፖሩል ሲያስቆጥሩ÷አቤል ማሙሽ ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል፡፡

እንዲሁም 12፡ 00 ላይ ኢትዮጵያ ቡናን እና መቻልን ባገናኘው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና 4 ለ 0 በሆነ የሰፊ ጎል ልዩነት ማሸነፍ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ጎሎች መስፍን ታፈሰ፣አብዱልከሪም ወርቁ፣ መሐመድ ኑር እና አንተነህ ተፈራ አስቆጥረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.