Fana: At a Speed of Life!

አቡበከር ናስር ካጋጠመው ጉዳት አገግሞ ወደ ሜዳ እንዲመለስ ድጋፋችን ያስፈልገዋል – አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አቡበከር ናስር ካጋጠመው ጉዳት አገግሞ ወደ ሜዳ እንዲመለስ ድጋፋችን ያስፈልገዋል ሲሉ የማሜሎዲ ሰንዳውንስ አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ገለፁ፡፡

አሰልጣኙ የአጥቂ መስመር ተጫዋቹን አቡበከርን አስመልከተው በሰጡት አስተያየት÷ አቡበከር ከኦርላንዶ ፓይሬትስ ጋር በነበረው ጨዋታ ያጋጠመው ጉዳት ከባድ መሆኑን አንስተዋል።

አቡበከር ናስር ካጋጠመው ከባድ እና የተወሳሰበ ጉዳት ጋር እየታገለ እንደሚገኝ የገለፁት አሰልጣኙ÷ በቅርቡ አገግሞ ቡድናቸውን እንደሚቀላቀል ያላቸውን እምነት ገልፀው፤ እኛ ልንሰጠው የምንችለውን ድጋፍ ልናደርግለት ይገባል ብለዋል፡፡

ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የአቡበከርን የረጅም ጊዜ ጉዳት ተከትሎ ከሳምንታት በፊት ተጨማሪ ተጫዋች ያስፈረመ ሲሆን፤ በዚህም አቡበከር ናስር ከክለቡ ጋር የሚኖረው ቆይታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ መግባቱ ተገልጿል፡፡

በደቡብ አፍሪካው ክለብ ሶስት የቁርጭምጭሚት ጉዳት ያስተናገደው አቡበከር ናስር፤ በቀጣይ ጊዜያት ከክለቡ ጋር ያለው ቆይታ ይወሰናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.