Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ክልል ዞኖች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ክልል ከሁሉም ዞኖች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

የዛሬው ስብሰባ በክልሉ ባለፉት ሣምንታት በብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች መሪነት የተደረገውን ውይይት ተከትሎ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በውይይቱ ተነስተው ምላሽ ከተሰጠባቸው ጉዳዮች ውስጥ የሰላም፣ የፀጥታ እና የልማት ፍላጎት ጉዳዮች እንደሚገኙበትም ነው ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ የሚያመላተው፡፡

የኅብረተሰብ ተወካይ ሽማግሌዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያላቸውን አድናቆት ለመግለፅ ባሕላዊ ስጦታ አበርክተውላቸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.