Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የ3 ሚሊየን ዶላር የሕክምና መርጃ መሣሪያ በድጋፍ አገኘች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤድ) ለኢትዮጵያ 3 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ 156 የቲቢ በሽታ መመርመሪያ መሣሪያዎችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

የዩ ኤስ ኤድ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ስኮት ሆክላንደር ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ አሜሪካ ድጋፏን ማጠናከሯን አንስተዋል፡፡
የዛሬው ድጋፍም ይህን ያሳያል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ የቲቢ በሽታ የምርመራ አቅምን በማጠናከር የበሽታውን ተዛማችነት ለመቀነስ እንደሚያግዝም ገልጸዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት÷ ድጋፉ የቲቢ በሽታ ምርመራን በቀላሉና ባጠረ ጊዜ በመመርመር የበሽታውን ሥርጭት ለመቀነስ ያስችላል ብለዋል፡፡

የሕክምና መሣሪያዎቹን ለሕክምና ተቋማት ተደራሽ የማድረጉ ሥራ በቅርቡ እንደሚጀመር ጠቁመው÷ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.