Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርና የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የ200 ሚሊየን ብር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር የ200 ሚሊየን ብር ስምምነት መፈራረሙን አስታወቀ፡፡

ስምምነቱ ፥ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በጋራ ለመስራት የሚያስችል እና ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚውል ከ200 መቶ ሚሊየን በላይ ብር ድጋፍን ያካተተ ነው።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርና የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ለበርካታ ዓመታት በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸውን የተናገሩት የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር ዋና ፀሀፊ ጌታቸው ተዓ ናቸው፡፡

ስምምነቱ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖችን ለመደገፍ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

የሁለትዮሽ ትብብሩና ድጋፉ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖችን ተደራሽ ለማድረግ ያስችላል ያሉት በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል እንደራሴ ኒኮላስ ቫንአክስ ፥ ድጋፉ ምንጊዜም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የተናገሩት።

በቅድስት አባተ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.