Fana: At a Speed of Life!

የገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት ተግባራዊ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦቪድ ግሩፕ የትራንስፖርት ችግርን መፍታት የሚያስችል የኬብል ካር (በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት) ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ ታደሰ ፥ ኦቪድ ግሩፕ በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘመናዊ ቤቶችን ከመገንባት ባሻገር የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት በአዲስ አበባ የኬብል ካር ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ የፕሮጀክት ጥናት ማጠናቀቁን ይፋ አድርገዋል።

የባቡር እና የመኪና መሰረተ ልማቶችን ማፍረስ ሳያስፈልግ በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት ወይም ኬብል ካር ቴክኖሎጂን በአዲስ አበባ ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል ነው ያሉት።

መንግስት የአቅመ ደካማና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ኑሮ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው ፥ ለስኬታማነቱ ኦቪድ እገዛና ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

በሁሉም የልማት መስኮች የመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱንም ጠቅሰዋል፡፡

በመሆኑም ኦቪድ ሀገራዊ ልማትን ከማገዝ ባለፈ በግንባታው ዘርፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የመጠቀምና በአጭር ጊዜ የማጠናቀቅ ስራውን ይቀጥላል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.