Fana: At a Speed of Life!

የግላኮማ ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ግላኮማ የዐይን ህመም በዐይን ነርቭ ላይ ችግር የሚያስከትል ሲሆን በዐይናችን ውስጥ የሚገኘው ግፊት በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ህመም ነው።

የዚህ ግፊት መጨመር በዐይናችን የምናያቸውን ምስሎች ወደ አንጎል የሚወስደውን የዐይናችንን ነርቭ ይጎዳል፤ ይህም በቀጣይነት ቋሚ ለሆነ የዐይን ብርሃን እጦት ይዳርጋል።

ግላኮማ በሚጀምርበት ጊዜ የሚያሳየው ቀዳሚ ምልክት ወይንም የህመም ስሜት ስለሌለ ማንኛውም ሰው መደበኛ የሆነ የዐይን ህክምና ማድረግ ይኖርበታል፡፡

የግላኮማ ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

በአብዛኛው ግላኮማ በቅድሚያ የህመም ምልክት ላያሳይ ቢችልም ከጊዜ በኋላ ግን የመጀመሪያ ምልክት የሚሆነው በጥግ በኩል የሚጀምር የአይን ብርሃን ችግር መሆኑን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከምልክቶቹ ውስጥ ድንገተኛ የሆነ የዐይን ህመም፣ ከፍተኛ የራስ ምታት፣ የዐይን ብዥታ፣ ጥርት ያለ እይታ አለመኖር፣ የዐይን መቅላት፣ የዐይን ብርሃን ማጣት እና የዐይን እይታ ጥበት ናቸው፡፡

እነዚህ ሁኔታዎች ሲያጋጥምዎ በአፋጣኝ ወደ ዐይን ሀኪም መሄድ ይጠበቅብዎታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.