Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች በጋራ ጉዳዮቻቸው ዙሪያ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሊበረታታ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች በጋራ ጉዳዮቻቸው ዙሪያ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሊበረታታ እንደሚገባ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) ገለጹ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ “ሴቶችን እናብቃ፣ ሰላምና ልማት እናረጋግጥ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የሚሲዮኑ አመራሮች፣ ሰራተኞች፣ የዳያስፖራ ተወካዮች እና የማህበራዊ ሚዲያ አካላት በተገኙበት በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድምቀት ተከብሯል።

በመርሀ ግብሩም የሚሲዮኑ መሪ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣውን የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ሁለንተናዊ ተሳትፎዎችን በሁሉም እርከኖች ይበልጥ ማጎልበት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በደቡብ አፍሪካ በርካታ ሴት ኢትዮጵያዊያን የሚገኙ ሲሆን፣ በሚሲዮኑ ክትትልና ድጋፍ በራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ እንዲደራጁ በማድረግ በጋራ ጉዳዮቻቸው ዙሪያ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ ሊበረታታ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ሴቶችን እንዲያቅፍና እንዲያሳትፍ የማድረጉ ጥረትም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አምባሳደሩ መግለጻቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የሚሲዮኑ ምክትል መሪ ወ/ሮ ደሴ አለባቸው በበኩላቸው ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን መከበር መነሻ የሴቶች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚኖሚዊና ማህበራዊ ተሳትፎ በርካታ ጥያቄዎችና ምክንያት መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ጥያቄዎቹም በጊዜ ሂደት ምላሽ እያገኙ ዛሬ ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል፡፡

ሴት የቤተሰብ፣ የማህበረሰብ፣ የሀገር ሁለንተናዊ ግንባታ መሰረት በመሆኗ እስከታችኛው የመንግስትና የተለያዩ የማህበረሰብ መዋቅሮች የሴቶችን ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.