Fana: At a Speed of Life!

የውጪ ምንዛሬ ፈቃድ ክልከላ በተጣለባቸው እቃዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ ማስተካከያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጪ ምንዛሬ ፈቃድ ክልከላ በተደረገባቸው እቃዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ ማስተካከያ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ የሰጠው ማብራሪያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

የውጪ ምንዛሬ ፈቃድ ክልከላ በተጣለባቸው እቃዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ የተደረገ ማስተካከያ፣

የውጭ ምንዛሬ ለመሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች፣ ለመድሃኒትና ለህክምና መሳሪያዎች፣ ከውጭ ገብተውበሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ገቢ ምርቶችን ለመተካት የሚውሉ ምርቶችን ለማምረትለሚውሉ ግብዓቶች፣ የካፒታል እቃዎችን፣ ወዘተ ለማስገባት ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መንግስት ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸውዝርዝር እቃዎችና ተሽከርካሪዎች በገንዘብ ሚኒስቴር በቀን 04/02/2015 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ለአፈጻጸም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ለጉምሩክ ኮሚሽን ተላልፎ በስራ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ይህን ተከትሎ ጉምሩክ ኮሚሽን በቀን 17/04/2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ በጠየቀው እና መንግስት በሰጠው አቅጣጫ መሰረት የውጭ ምንዛሬ ክልከላ ከተደረገባቸው እቃዎች ጋር ተያይዞ በአፈጻጸም ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመዳሰስና በመለየት የሚከተለው ማስተካከያተደርጓል፡፡

1. ከገንዘብ ሚኒስቴር በቁጥር ክሂገ1/7/252 በቀን 04/02/2015 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ በሠንጠረዥ የተገለጹት የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ዝርዝሮች በሕግ በተደነገገ ፍራንኮ ቫሉታ የሚገቡ እቃዎችን እና ተሽከርካሪዎችን የማይመለከት መሆኑን፤

2. ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም በፊት የባንክ ፈቃድ የተሰጠባቸው እቃዎች እና ተሽከርካሪዎች በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል የሚቀርቡ ሠነዶች አስፈላጊው ማጣራት እየተደረገባቸው ለመጨረሻ ጊዜ በመሸጋገሪያ እንዲገቡ፤

3. ተሽከርካሪዎች ጎረቤት ሀገር ወደብ ወይም ጉምሩክ ጣቢያ በደረሱበት ጊዜ በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ (ማሻሻያ) ቁጥር 1287/2015 አንቀጽ 2(24) ለአዲስ ተሽከርካሪ የተሰጠውን ትርጉም የሚያሟሉ ሆነው ነገር ግን ይህን ውሳኔ ሲጠብቁ የተሽከርካሪው እድሜ ያገለገለ ምድብ ውስጥ የገባባቸው ከሆነ በክልከላው ምክንያት በጎረቤት አገር ወደብ ወይም በጉምሩክ ጣቢያየቆዩበት ጊዜ ሳይታሰብ እድሜው ጎረቤት አገር ወደብ ወይም የጉምሩክ ጣቢያ እስከደረሰበት ያለውን ጊዜ ድረስ ብቻ በማስላት እንዲስተናገዱ፤

4. የቀረጥ ነፃ ሱቆች የሚያስመጧቸው ዕቃዎች የውጭ ምንዛሪ ክልከላው እንዳይመለከታቸው፤

5. ከታች በሠንጠረዥ የተመለከቱ ዝርዝሮች አፈጻጸማቸው በእቃው ዓይነት መግለጫ መሰረት እንዲሆን፣

6. ተሽከርካሪን ሳይጨምር የውጭ ምንዛሬ ክልከላው የሚመለከተው እቃዎቹ አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ምንም ዓይነት ተጨማሪ ዝግጅት ሳይደረግባቸው ወይም የምርት ሂደት ሳይከናወንባቸው ወደ አገር በገቡበት ሁኔታ በቀጥታ ጥቅም (አገልግሎት) ላይ እንዲውሉ የተዘጋጁ ምርቶችን ብቻ ሲሆን፣ ማናቸውንም ለምርት ግብዓት የሚሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወይም ግብዓቶችን ክልከላው የማይመለከት መሆኑን፣

7. ተሽከርካሪን በሚመለከት ከተዘጋጀው በከፊል የተበተነ (SKD) ወይም ሙሉ በሙሉ የተበተነ (CKD) መስፈርት በታች የሆኑ (መስፈርቱን የማያሟሉ) ከሆነ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው መሆኑን፣ እየገለጽን፤ ከገንዘብ ሚኒስቴር በቁጥር ክሂገ1/7/252 በቀን 04/02/2015 ዓ.ም የተጻፈው ደብዳቤ እና በተለያየ ጊዜ የተሰጡ ማብራሪያዎች ተሽረው በዚህ የተተኩ ሲሆን፣ በአፈጻጸም ወቅት ሲያጋጥሙ የነበሩ ችግሮች ከላይ በቀረበው ማብራሪያ እና አባሪ በተደረገው 03 ገጽ (ከታች በሠንጠረዥ በተመለከቱ ዝርዝሮች) ማስተካከያ መሰረት ተፈጻሚ እንዲሆን እንገልጻለን፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.