Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በዓድዋ ድል መታሰቢያ የገነባውን ማዕከል አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ለደምበኞቹ  ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጅዎች የሚያሳይና ጎብኝዎች በተግባር የሚሞክሩበት ማዕከል በዓድዋ ድል መታሰቢያ አስመርቋል፡፡

ማዕከሉ ኢትዮ ቴሌኮም ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያለፈበትን የቴክኖሎጅ ጉዞ የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ደንበኞች የተቋሙን ምርትና አገልግሎት የሚመለከቱበት፣ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በተግባር በመሞከር ፈጠራቸውን የሚያሳድጉበትና የቴክኖሎጂ ግኝቶችን የሚመራመሩበት መሆኑም ተመላክቷል።

የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በምረቃው ላይ እንዳሉት÷ ማዕከሉ እጅግ ፈጣን የአምስተኛው ትውልድ (5 ጂ) ኮኔክቲቪቲ፣ ቨርቹዋል ሪያሊቲ፣ የፈጠራ ሶልሽኖች፣ የስማርት ሆም አውቶሜሽን እና የቴሌብር ግብይቶችን በውስጡ ይዟል።

ኢትዮ ቴሌኮም የቴክኖሎጅ ፈጠራን የሚያሳድጉ ሥራዎችን ማከናወኑን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.