Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የተበጀተለትን የቄጦ የወንዝ መቀልበሻና መስኖ ልማት ግንባታ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የተበጀተለትን የቄጦ የወንዝ መቀልበሻና መስኖ ልማት ግንባታ በሚቀጥለው ዓመት ሕዳር ወር ላይ ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ባለቤትነት በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን በሰዲ ጨንቃና ሃዋ ገላን ወረዳዎች የሚካሄደው ፕሮጀክቱ የተጀመረው ታኅሳስ 2014 ዓ.ም ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ የቄጦ ወንዝ ውሃን በመጠቀም 2 ሺህ 500 ሄክታር በማልማት በሁለቱም አቅጣጫ 5 ሺህ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ በማድረግ በዓመት ሦስት ጊዜ በማምረት ምርታማነትን ማሳደግ እንደሆነ ተነግሯል።

የቄጦ የወንዝ መቀልበሻና መስኖ ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ የካቲት ወር 2016 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ 11 በመቶ መከናወኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሮጀክቱን በስራ ተቋራጭነት የሚገነባው ሃቨሪም ኮንስትራክሽን ጄኔራል ኮንትራክተር ሲሆን፥ የማማከሩን ስራ የሚሰራው ደግሞ ኢንሲራድ ሲቪል ሲስተም ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ. የግል ማህበር ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.