Fana: At a Speed of Life!

ኢንስቲትዩቱ በአፋር ክልል የተሰጠውን ምርጥ ዘር የማቅረብ ሃላፊነት እየተወጣ ነው – አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር የምርምር ኢንስቲትዩት ምርጥ ዘር በማቅረብ ረገድ የተሰጠውን ሃላፊነት እየተወጣ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ÷ የአፋር አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር የምርምር ኢንስቲትዩት በምርምር በማውጣት እያባዛ ያለውን የስንዴ ምርጥ ዘር ማሳ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት÷ ኢንስቲትዩቱ አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎለት ምርጥ ዘር በማቅረብ ረገድ የተሰጠውን ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ ነው።

በቀጣይም መሬት እና ውሃን በአግባቡ በመጠቀም ከዚህ በበለጠ በምርምሩም ሆነ በኢንተርፕራይዞች የሚሰሩ ስራዎችን ማስፋት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

የአፋር ክልል አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ምርጥ ዘር እያመረተ መሆኑን አስታውሰው÷ አሁን ላይ ክልሉ ምርጥ ዘር አዘጋጅቶ ለሌሎችም ጭምር በማቅረብ እየታወቀ መጥቷል ብለዋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ነኢማ መሐመድ በበኩላቸው÷ ማዕከሉ በበጀት ዓመቱ 230 ሄክታር መሬት ላይ የምርጥ ዘር ስንዴ በማልማት ላይ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በኢንስቲትዩቱ የሰብል ምርምር ዳይሬክተር አቶ ዳውድ ታከለ÷ በኢንስቲትዩቱ ተመርጦ እየተመረተ ያለው ስንዴ በሽታዎችን የመከላከል አቅም ያለው መሆኑን ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.