Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ም/ርዕሰ መሥተዳድር ከታይዋን የገበያ ማዕከል ተጎጂዎች መልሶ ማቋቋም ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ኢብራሂም ኡስማን ከጅግጅጋ ከተማ ታይዋን የገበያ ማዕከል ተጎጂዎች መልሶ ማቋቋም ኮሚቴ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በጅግጅጋ ከተማ ታይዋን የገበያ ማዕከል ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ሀብት ንብረታቸውን ያጡ ነጋዴዎችን ለማቋቋም እስካሁን የተከናወኑ ሥራዎች ሪፖርት ቀርቧል፡፡

ለተጎጂዎች የተደረገው ድጋፍ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ የጅግጅጋ ከተማ ታይዋን የገበያ ማዕከል የተጎጂዎች ሀብት አሰባሳቢና መልሶ ማቋቋም ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትም አቶ ኢብራሂም አዳምጠዋል።

በቀጣይም ለነጋዴዎቹ የሚደረገውን ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር መደረጉን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለማከናወን የታቀዱ ዕቅዶችን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሠራ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድሩ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.