Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ተቋማት የስኬት ሽልማት ትብብርና ተወዳዳሪነትን የሚያጎለብት ነው- የተሸላሚ ተቋማት አመራሮች

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ተቋማት የስኬት ሽልማት ትብብርና ተወዳዳሪነት የሚያጎለብት መሆኑን የተሸላሚ ተቋማት አመራሮች ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል።

ሽልማቱ የተበረከተው ለግብርና ሚኒስቴር በስንዴ ልማት ፕሮግራም ፣ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ለኢትዮጵያ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ነው፡፡

የተሸላሚ ተቋማት አመራሮች እንዳሉት÷ እውቅናው ይበልጥ እንዲሰሩ ከማነሳሳቱም በላይ ለሌሎች ተቋማት አርአያነትን የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ክፍሌ ሆሮ(ኢ/ር)÷ ሽልማቱ ሁሉም ተቋማት በተሰማሩበት መስክ ተግተው እንዲሰሩ መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው÷ ሽልማቱ ለተቋሙ ስኬት ቀን ከሌት ለሚሰሩ ሰራተኞች ሞራል የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

እውቅናው ሌሎች ተቋማትም ስኬታማ ለመሆን እንዲሰሩ በማድረግ በአገር አቀፍ ደረጃ ጠንካራ ተቋማትን ለመፍጠር እንደሚያግዝም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው÷ሽልማቱ ለተመዘገቡ ስኬቶች እውቅና ከመስጠቱም በላይ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለማከናወን መነሳሳትን የሚፈጥር ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ ÷ ሽልማቱ ለመላ ኢትዮጵያውያን አርሶ እና አርብቶ አደሮች ጭምር እውቅና የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.