Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከካናዳ ፓርላማ ጸሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፓርላማ ጸሃፊ ሮበርት ኦሊፋንት ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው አምባሳደር ታዬ÷ ካናዳ በአስቸጋሪ ጊዜያት  ለኢትዮጵያ  እያደረገች ያለውን ዘርፈ ብዙ  ድጋፍ አድንቀው ÷ የሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የሁለቱን ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ማሳደግ ያስፈልጋል ያሉት አምባሳደር ታዬ÷ የካናዳ ባለሀብቶች  በዲጂታል ዘርፍ፣ በማዕድን፣ በኢነርጂ እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ሮበርት ኦሊፋንት በበኩላቸው÷ በካናዳ የውጭ ግንኙነት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ገልጸዋል።

አክለውም ካናዳ ከኢትዮጵያ ጋር በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በሰብአዊ እርዳታ፣ በልማት ትብብር እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች ግንኙነቷን ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

ከሁለትዮሽ ግንኙነት በተጨማሪ ሁለቱ ወገኖች የጋራ ጉዳዮች በሆኑ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ  ጉዳዮች ላይ ምክክር ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.