Fana: At a Speed of Life!

በጀልባ ወደ ጣልያን ሲጓዙ የነበሩ 50 ስደተኞች ሕይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀልባ ከሊቢያ ወደ ጣልያን ሲጓዙ የነበሩ 50 ስደተኞች ሕይወት አልፏል፡፡

ይህን የገለጹት በአደጋው ሕይወታቸው ካለፉ ሰዎች ጋር አብረው የነበሩና ከአደጋው የተረፉ ስደተኞች ናቸው ተብሏል፡፡

ከአደጋው የተረፉት 25 ሰዎች መካከል ሁለቱ ራሳቸውን ስተው እንደሚገኙና በጣልያን መንግስት ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡

የተቀሩት 23 ሰዎች ደግሞ በጀልባው በነበረው ነዳጅ በከባድ ሁኔታ የተቃጠሉ፣ የደከሙ፣ በውሃ ጥም ለድርቀት የተጋለጡ እንደሆኑ ተሰምቷል፡፡

በሜዲትራኒያን የነፍስ አድን ተቋም ቃል አቀባይ ፍራንሴስኮ እንደተናገሩት ፥ በሕይወት የተረፉት ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ፥ 12ቱ ለአካለ መጠን ያልደረሱና ሁለቱ ደግሞ ለአስራዎቹ እድሜ እንኳን የደረሱ አይደለም ፡፡

ስደተኞቹ የሴኔጋል፣ ማሊ እና ጋምቢያ ተወላጆች እንደሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡

ክሬዞ እንዳሉት ፥ በሕይወት የተረፉት ሰዎች በጭንቀት ተውጠው በጉዞው ወቅት ስለተፈጠረው ነገር ሙሉ መረጃ መስጠት እንኳን እንዳልቻሉ ማንሳታቸውንም አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል፡፡

በባሕር ላይ የሞቱ እና የጠፉትን ሰዎች ቁጥር ለማወቅ የሰብዓዊ ድርጅቶች ብዙውን ጊዜ በሕይወት የተረፉ ሰዎች ቃል ላይ ተመስርተው ይናገራሉ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) እንደገለጸው፥ በዚህ ዓመት እስከ ፈረንጆቹ መጋቢት 11 ድረስ 227 ሰዎች በመካከለኛው ሜዲትራኒያን ሞተዋል፡፡

ከሞት የተረፉ ሰዎች እንዳሉት፥ ጀልባዋ ከሊቢያ ዛዊያ ስትነሳ 75 ሰዎች ሴቶች እና አንድ ታዳጊ ህጻንን ጨምሮ ተሳፍረው ነበር፡፡

ከመነሻው ብዙም ሳይቆይ ሞተሩ በመበላሸቱ ምክንያት አደጋው ደርሷል ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.