Fana: At a Speed of Life!

የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በሲስተም ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን አገልግሎቶት መስጠት መጀመራቸው ተገልጿል፡፡

ባንኩ በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቅርንጫፎች አገልግሎት የጀመረ መሆኑን  ለደንበኞቹ  አስታውቋል፡፡

የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጡም ነው የተገለጸው፡፡

በተመሳሳይ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን (ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ሞባይል ባንኪንግ፣ እንዲሁም ሲቢኢ ብር) ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎልም ባንኩ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

በቅርንጫፎች፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ በሞባይል ባንኪንግ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ ማጋጠሙን ባንኩ መግለጹ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.