Fana: At a Speed of Life!

በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ጋና ገባ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የሚሳተፈው ከ90 በላይ ሰዎችን ያካተተው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት ጋና አክራ ገብተዋል።

ልዑኩ ከአጭር እስከ መካከለኛ ርቀት የሚወዳደሩ አትሌቶች እና የሴቶች የቅርጫት ኳስ ቡድንን ያካተተ ነው፡፡

በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱም በጋና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ ፍቅሬ ጎሳዬን ጨምሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ተገኝተዋል።

አምባሳደሩም ለልዑካን ቡድኑ አባላት የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ÷ የአበባ ስጦታ አበርክተዋል።

እስካሁን ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው  አንድ የብር ሜዳልያ ማግኘቷ ይታወቃል፡፡

በሰለሞን በቀለ

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.