Fana: At a Speed of Life!

ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣናን ጨምሮ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ100 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጠረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣናን ጨምሮ በ12 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ100 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው ዜጎች መካከልም ከ75 በመቶ በላይ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ይህም የሥራ ዕድል ፈጠራው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደ ሀገር እየተሠራ ያለውን ሥራ ውጤታማነት ያሳያል መባሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.