Fana: At a Speed of Life!

በዩኒቨርሲቲዎች እየተተገበሩ ያሉ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የዘርፉ ኃላፊዎች በትጋት እንዲሠሩ ተጠየቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እየተተገበሩ ያሉ ቁልፍ የለውጥ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የዘርፉ ኃላፊዎች በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡

“ከፍተኛ ትምህርት ከፍ ላለ ተጽዕኖ” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ የቆየው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች ፎረም ተጠናቅቋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ኮራ ጡሽኔ÷ በከፍተኛ ትምህርት ላይ እየተተገበሩ ያሉ ቁልፍ የለውጥ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የዘርፉ ኃላፊዎች በትኩረት በመሥራት የድርሻቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በፎረሙ በተጀመሩ የለውጥ መርሐ-ግብሮች አተገባበር፣ የለውጥ ስኬቶችና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን÷ የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች እና የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በፎረሙ ላይ መሳተፋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.