Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግዛው ተ/ማርያም (ኢ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግዛው ተክለማርያም (ኢ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ከኢትዮጵያ ስፖርት ጋር ሰፊ ትስስር ያላቸው ግዛው (ኢ/ር) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ከ1988 እስከ 1996 በፕሬዚዳንትነት መርተዋል፡፡

እንዲሁም በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የፋይናንስ ኮሚቴ አባል በመሆን ማገልገላቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ ተቋማትን በኃላፊነት ከመምራታቸው ባሻገር÷ የሙገር ሲሚንቶ ስፖርት ክለብ እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በግዛው ተክለማርያም (ኢ/ር)  ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰብ እና ለእግር ኳሱ ቤተሰብ መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.