Fana: At a Speed of Life!

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቆላ ሼሌ ቀበሌ ዶንቤ በተባለ ስፍራ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ ሹፌሩን ጨምሮ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

አደጋው ትናንት ምሽት በግምት 2፡00 ሠዓት አካባቢ መከሰቱን የገለጹት የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ደበበ ኦንታ÷ ከሟቾች በተጨማሪ በስድስት ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በአካባቢው በሚገኝ ጤና ተቋም የሕክምና ዕርዳታ ተደርጎላቸው ወደቤታቸው መሸኘታቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

አደጋው የተከሰተውም አንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከገረሰ ወደ አርባምንጭ በመጓዝ ላይ እያለ ተንሸራትቶ በመገልበጡ ነው ብለዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመው÷ አሽከርካሪዎች የየአካባቢውን መልክዓ ምድርና የአየር ሁኔታ ተረድተው በኃላፊነትና በጥንቃቄ ማሽከርከር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.