Fana: At a Speed of Life!

የታንዛኒያ ወታደራዊ ልዑክ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ12 ሀገራት በላይ ተማሪዎችን ያካተተው የታንዛኒያ ወታደራዊ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የሚያከናውናቸውን የትምህርት፣ የጥናትና የምርምር መርሐ ግብሮችን ጎበኘ።

በዩኒቨርሲቲው የሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ አዛዥ ኮሎኔል ተገኝ ደጀኔ (ዶ/ር) የሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ግንኙነት ዘርፈ ብዙ ወታደራዊ ትብብሮችን የሚያጠናክር ከመሆን ባሻገር ስኬታማ ልምዶችን የሚያሳድግ ነው ብለዋል።

ሀገራቱ በተለያዩ ወታደራዊ ዘርፎች ላይ ግንኙነታቸውን አጠናክረው በትጋት በመስራት የዘመኑን ቴክኖሎጂ በጋራ መጠቀም የሚያስችል ጠንካራ ልምድ በመለዋወጥ ተደራሽ የሆነ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።

ዩኒቨርሲቲው ተጓዳኝ የመሰረተ ልማት ገፅታዎችን ጨምሮ ሁለንተናዊ የመማር ማስተማር ተልዕኮና እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን ለቡድኑ ገለፃ ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የውጭ ግንኙነትና ተቋማት ትብብር ዳይሬክተር ሻለቃ በተለይ ተካ (ዶ/ር) ናቸው።

በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን የገለፁት የልዑካን ቡድኑ አባላት፤ ዩኒቨርሲቲው ከሚሰጠው የአጭርና የረዥም ጊዜ የትምህርት መርሐ ግብሮች ተጨባጭ ልምድ እንደያዙ መናገራቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.