Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት የኢፍጣር መርሐ ግብር በወንድም ካሊድ ምግባረ ሠናይ ፋውንዴሽን ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት የኢፍጣር መርሐ ግብር በወንድም ካሊድ ምግባረ ሠናይ ፋውንዴሽን ተካሄደ።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች፣ የእምነት አባቶች፣ አማኞች፣ አርቲስቶች፣ በማዕከሉ ድጋፍ የሚደረግላቸውና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በመርሐ-ግብሩ ላይ፤ መልካም ልብ እንደ ወንድም ካሊድ ማብዛት ከቻልን ተቸግረው ጎዳና ላይ የሚወጡ ወገኖች አይኖሩም ነበር ብለዋል።

የጀመርነውን የዐቢይና የረመዳን ጾም በተጀመረው መተሳሰብና መደጋገፍ እንዲያልቅ እየታየ ያለው ኢትዮጵያዊ ባህል መሠረቱ እየተጠናከረ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያዊያውያን በተለይ በኃይማኖት ሳይለያዩ አብሮነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለሌሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲበረከቱና ዜጎች ከራስ አልፈው ያላቸውን ዕውቀትና አቅም እንዲለግሱም ጥሪ አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.