ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ለሆነ የልማት መፍትሔ መሠረት ለመጣል በፅናት መቆሟን አረጋገጡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ለሆነ የልማት መፍትሔ መሠረት ለመጣል በፅናት መቆሟን አረጋገጡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የምዕራብ ኦሞ ዞንን መጎብኘታቸውን እና በዚህም የተሰማቸውን ደስታ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
አካባቢው የተፈጥሮ ውበት እና እምቅ ሀብት ሞልቶ የፈሰሰበት መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
በትክክለኛ የልማት ድጋፍ እና የሰላም ከባቢ ሁኔታ ለኢትዮጵያ የእድገት ርምጃ በእጅጉ አስተዋፅዖ የሚያደርግ አካባቢ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
ምንም እንኳ ሁሉንም የልማት ፍላጎት ማሟላት ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም÷ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ለሆነ የልማት መፍትሔ መሠረት ለመጣል በፅናት መቆሟን ለአካባቢው ሕዝብ አረጋግጫለሁ ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን ያደረጉት ጉብኝት÷ ባለፉት ሣምንታት ያደረጓቸውን ውይይቶች መነሻ ያደረገ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡