የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሥተዳድር ም/ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት በ10ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡
መሥተዳድር ምክር ቤቱ የክልሉ ተቋማት 17 ማቋቋሚያና ማስፈፀሚያ ደንቦች ላይ ከተወያየ በኋላ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚሁ መሠረት የቀረቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን በመገምገም የሚኖራቸውን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት እንዲሁም የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግርን ብሎም ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያበረክቱትን ፋይዳ በመገንዘብ ውሳኔ ማሳለፉ ተመላክቷል፡፡