Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው ለታላቁ ህዳሴ ግድብ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳያስፖራው ማህበረሰብ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር ከተለያዩ የመንግሥት አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

ውይይቱ ዳያስፖራው ማህበረሰብ በልማት እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎውን እንዲያሳድግ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

በውይይቱ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎትና ከሌሎች ተቋማት የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች ታድመዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) እንደተናገሩት÷ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አሁን ላይ ከ95 በመቶ በላይ ደርሷል።

ግድቡ አሁን ለደረሰበት ደረጃ የዳያስፖራው ተሳትፎ የላቀ ሚና መጫወቱን ጠቅሰው ÷ዳያስፖራው በዲፕሎማሲ፣ በቦንድ ግዥና በሌሎች መስኮች ያበረከተው ድጋፍ ወሳኝ እንደነበር ተናግረዋል።

ግድቡ አሁንም ቀሪ ሥራዎች ያሉት በመሆኑ የዳያፖራው ማሕበረሰብ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር በላይነህ አቅናው በበኩላቸው÷ አገልግሎቱ ዳያስፖራው በሀገሩ ልማት ላይ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር እየሰራ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የዳያስፖራ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑንም አመልክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.