ምክር ቤቱ የዒድ አል-ፈጥር በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሣችሁ መልዕክት አስተላለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ሺህ 445ኛውን የዒድ አል-ፈጥር በዓልን በማስመልከት ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሣችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
በመልዕክቱ ÷ የዒድ አል-ፈጥር በዓል የሠላም የመረዳዳትና የመተሳሰብ መገለጫ ሆኖ እንዲያልፍ መልካም ምኞቱን ገልጿል ።
ሕዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ሠላምና አንድነት ለማፅናት የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለመረጋገጥ እያበረከተ ያለውን ዘርፈ ብዙ አስተዋጽዖ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ምክር ቤቱ አሳስቧል ።